የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church - ግኑኝነት ስለማድረግ ይሆናል።

ከወላይታ እና አከባቢ ክልል ሶዶ ከተማ ቂራ አጥቢያ ሙወቤ አሁን የያዘችው ይዞታ 400 ካሬ ብቻ በመሆኑ እጅግ ጠቦናል። በመሆኑም ጌታ ፈቃዱ ሆኖ ሁለት ድንበርተኞች ቤታቸውን እንድንገዛ ጠይቆናል።ተጨማሪ ቦታዎችን ሁለቱን ብንገዛ ምርጫ የሌለው ጉዳይ ሆኖ ሳለ ግን በአቅም ማነስ ምክንያት አንዱን ቢናጣም ከሁለት አንዱን ለመግዛት በመወሰን በጸሎት ላይ እንገኛል። ስለዚህም አስፈላጊ ብር ብድር ለማግኘት ከብርሐን ባንክ ጋር ውል ለማከናወን አስፈላጊው ሁሉ ተጠናቅቆ የእናንተ ድጋፍ ደብዳቤ ብቻ አስፈልጎናል። ስለዚህ ሰው ተወክሎ ወደዛ መሄድ አለበት ወይስ ሌላ የመገነኛ ዜዴ አላችሁ። አመሰግናለሁ ። የአጥቢያይቱ ሽማግሌዎች ስብስብ ም/ ሰብሳቢ ይልማ ነኝ።